ጽንስን ለማስወረድ ሁለት አይነት መድሐኒቶች አሉ፦ ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል። የኪኒን ጽንስ ማስወረጃ በተሻለ ሁኔታ የሚሰራው ሁለቱም እነዚህ መድሐኒቶች አብረው ከተወሰዱ ነው። ይሁንና፣ ሚፈፕሪስቶን የማይገኝ ከሆነ ሚሶፕሮስቶል ብቻው እርግዝናን ለማቋረጥ ይሰራል፣ እንዲህም ሆኖ ጥንቃቄ ያለው ነው።
በሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ወይም ደግሞ በሚሶፕሮስቶል ብቻ ጽንስን በጥንቃቄ የምታወርጂባቸው መመሪያዎችን ትፈልጊ እንደሆነ ምረጪ።
ከመጀመርሽ በፊት ኪኒኖቹን መጠቀም ከመጀመርሽ በፊት ላይ ያለው ምክራችንን አንብቢ። የሚከተሉትን አረጋግጪ፦
በሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ጽንስን ለማስወረድ ውርጃ አንድ ባለ200 ሚግ ሚፈፕሪስቶን እና ከአራት እስከ ስምንት 200 ማይክሮግራም ሚሶፕሮስቶል መውሰድ ይኖርብሻል። እንዲሁም ህመምን ለማስታገስ እንደ ኢቡፕሮፈን ያለ የህመም ማስታገሻ ኪኒን አጠገብሽ ቢኖር ይሻልሻል። አሰታሚኖፈን እና ፓራሴታሞል በጽንስ ማስወረድ ጊዜ ለሚኖር ህመም አይሰሩም፣ ስለዚህ አይመከሩም።
እርግዝናን ለማቋረጥ ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል እንዴት አብረው እንደሚወሰዱ እነሆ፦
አንድ ባለ200 ሚግ ሚፈፕሪስቶን ኪኒን በውሃ ዋጪ።
24-48 ሰዓታት ጠብቂ።
4 ሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን (እያንዳንዳቸው 200 ማይክሮግራም) ከምላስሽ ስር አድርጊያቸውና እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው። በእነዚህ 30 ደቂቃዎች ጊዜ ውስጥ መናገር ወይም መብላት የለብሽም፣ ስለዚህ የማትረበሺበት ጸጥ ያለ ቦታ ላይ ብትሆኚ ተመራጭ ነው። ከ30 ደቂቃዎች በኋላ የተወሰነ ውሃ ጠጪና ከኪኒኖቹ የቀረውን ሁሉ ዋጪ። እንዲሁም መሸማቀቅ በቅርቡ የሚጀምር ስለሆነ እንደ ኢቡፕሮፈን ያለ ህመም አስታጋሽ የምትወስጂበት ጥሩ ጊዜ ነው።
4ቱ የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖቹን በወሰድሽ በ3 ሰዓታት ውስጥ መድማት እና መሸማቀቅ መጀመር አለበት።
4ቱ የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖቹን ከወሰድሽ ከ24 ሰዓታት በኋላ መድማት ካልጀመርሽ፣ ወይም ደግሞ ጽንስ ማስወረዱ መሳካቱን እርግጠኛ ካልሆንሽ 4 ተጨማሪ የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖቹን ከምላስሽ ስር አድርጊያቸው። እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው ከ30 ደቂቃዎች በኋላ የተወሰነ ውሃ ጠጪና ከኪኒኖቹ የቀረውን ሁሉ ዋጪ።
ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ከወሰድሽ በኋላ ምን እንደምትጠብቂ እወቂ። እዚህ
መጥፎ መሸማቀቅ ካጋጠመሽ ኢቡፕሮፈን ህመሙን የሚያስታግስ ጥሩ መድሐኒት ነው። በአብዛኛዎቹ አገሮች ባለ200 ሚግ ጥንካሬ ኢቡፕሮፈን ከመድሐኒት ቤት መግዛት ትችያለሽ (ያለሐኪም ትዕዛዝ)። በየ6-8 ሰዓታት 3-4 ኪኒኖችን (እያንዳንዳቸው 200 ማይክሮግራም) ውሰጂ። ህመምን ለማስታገስ ተጨማሪ ነገር ካስፈለገሽ እንዲሁም በየ6-8 ሰዓታት 2 ታይለኖል (325 ሚግ) ኪኒኖችን መጠቀም ትችያለሽ።
የጽንስ ማስወረድ ሂደቱ ካሳሰበሽ እና ተጨማሪ ድጋፍ የምትፈልጊ ከሆነ safe2choose.org, womenhelp.org ወይም womenonweb.org ላይ አጋሮቻችንን ማግኘት ትችያለሽ።
የጽንስ ማስወረጃ ኪኒኖቹን ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ከተጠቀምሽ ለሕክምና ክትትል የጤና ጣቢያ መጎብኘት የማስፈለግ ዕድሉ አነስተኛ ነው። እነዚህ መድሐኒቶች በጣም ውጤታም ከመሆናቸው የተነሳ የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ክትትል ያስፈልግሻል ብሎ የሚመክረው የሚከተሉት ከተከሰቱ ብቻ ነው፦
ከመጀመርሽ በፊት ኪኒኖቹን መጠቀም ከመጀመርሽ በፊት ላይ ያለው ምክራችንን አንብቢ። የሚከተሉትን አረጋግጪ፦
ሚፈፕሪስቶን በሁኔታሽ ላይ የማይገኝ ከሆነ እርግዝናን ለማቋረጥ ሚሶፕሮስቶልን ብቻ መጠቀም ትችያለሽ።
ሚሶፕሮስቶል ብቻ በመጠቀም ጽንስን ለማስወረድ አስራ ሁለት ባለ200 ማይክሮግራም ሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን መውሰድ ይኖርብሻል። እንዲሁም ህመምን ለማስታገስ እንዲረዳ የህመም ማስታገሻ አጠገብሽ ቢኖር ይሻላል። አሰታሚኖፈን እና ፓራሴታሞል ጽንስ በሚወርድበት ጊዜ ህመምን ለማስታገስ ስለማይሰሩ አይመከሩም።
እርግዝናን ለማቋረጥ ሚሶፕሮስቶል ብቻውን እንዴት እንደምትጠቀሚበት እነሆ፦
4 ሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን (እያንዳንዳቸው 200 ማይክሮግራም) ከምላስሽ ስር አድርጊያቸውና እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው። በእነዚህ 30 ደቂቃዎች ጊዜ ውስጥ መናገር ወይም መብላት የለብሽም፣ ስለዚህ የማትረበሺበት ጸጥ ያለ ቦታ ላይ ብትሆኚ ተመራጭ ነው። ከ30 ደቂቃዎች በኋላ የተወሰነ ውሃ ጠጪና ከኪኒኖቹ የቀረውን ሁሉ ዋጪ። እንዲሁም መሸማቀቅ በቅርቡ የሚጀምር ስለሆነ እንደ ኢቡፕሮፈን ያለ ህመም አስታጋሽ የምትወስጂበት ጥሩ ጊዜ ነው።
3 ሰዓታትን ጠብቂ።
ሌላ 4 የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን (200 ማይክሮግራም) በምላስሽ ስር አድርጊያቸውና እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው
ተጨማሪ 3 ሰዓታትን ጠብቂ።
ሌላ 4 የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን (200 ማይክሮግራም) በምላስሽ ስር አድርጊያቸውና እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው።
ኪኒኖቹን እየወሰድሽ ሳለ መድማት እና መሸማቀቅ መጀመር አለብሽ። ሁሉንም ከመውሰድሽ በፊት መድማት ብትጀምሪም እንኳ ሁሉንም 12 ኪኒኖች መውሰድሽን አረጋግጪ።
ሚሶፕሮስቶልን ከወሰድሽ በኋላ ምን መጠበቅ እንዳለብሽ እወቂ። እዚህ
መጥፎ መሸማቀቅ ካጋጠመሽ ኢቡፕሮፈን ህመሙን የሚያስታግስ ጥሩ መድሐኒት ነው። በአብዛኛዎቹ አገሮች ባለ200 ሚግ ጥንካሬ ኢቡፕሮፈን ከመድሐኒት ቤት መግዛት ትችያለሽ (ያለሐኪም ትዕዛዝ)። በየ6-8 ሰዓታት 3-4 ኪኒኖችን (እያንዳንዳቸው 200 ማይክሮግራም) ውሰጂ። ህመምን ለማስታገስ ተጨማሪ ነገር ካስፈለገሽ እንዲሁም በየ6-8 ሰዓታት 2 ታይለኖል (325 ሚግ) ኪኒኖችን መጠቀም ትችያለሽ።
የጽንስ ማስወረድ ሂደቱ ካሳሰበሽ እና ተጨማሪ ድጋፍ የምትፈልጊ ከሆነ safe2choose.org, womenhelp.org ወይም www.womenonweb.org ላይ አጋሮቻችንን ማግኘት ትችያለሽ።
ሚሶፕሮስቶልን ከተጠቀምሽ ለሕክምና ክትትል ጤና ጣቢያ መጎብኘት የማስፈለግ ዕድሉ አነስተኛ ነው። እነዚህ መድሐኒቶች በጣም ውጤታም ከመሆናቸው የተነሳ የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ክትትል ያስፈልግሻል ብሎ የሚመክረው የሚከተሉት ከተከሰቱ ብቻ ነው፦
ይህ ድር ጣቢያ በአግባቡ መስራት እንዲችል ስም-አልባ ኩኪዎች እና የተለያዩ የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶች ሊያስፈልገው ይችላል። የእኛን ደንቦችና ሁኔታዎች እና የግላዊነት መመሪያዎች ማንበብ ይችላሉ። ይህን ጣቢያ መጠቀሙን በመቀጠልዎ እኛ ይህን እንድናደርግ ፈቃድዎን እየሰጡን ነው።'